የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የቀለም ቅብ እና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ሊያሠራው ለፈለገው ሥራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሠሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

Description

ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም 

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የቀለም ቅብ እና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ሊያሠራው ለፈለገው ሥራ በግንባታ ዘርፍ ላይ የሚሠሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች፣ የሰው ኃይል በማቅረብ የሚሠሩ በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆንም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር ትችላላችሁ።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኃል።

2. በዘርፉ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

3. ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገበ የምስክር ወረቀት ያላቸው

4. ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና በአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በት/ቤቱ ግቢ ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር G+l/008 በመምጣት ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO 10,000 (አስር ሺ ብር ብቻ) በት/ቤቱ ስም በማሠራት ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. አሠሪው በት/ቤቱ አሸናፊ ካሸነፈበት አጠቃላይ የሥራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባት በፊት የተጫራቾች መመሪያ (instruction to bidder (TB) እንዲያነቡ እና የጥገና እና ዕድሳት ሳይት እንዲመለከቱ ይገደዳሉ።

9. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናሻያል ሰነድ አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገው ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱ ማህተብ እና የሚወዳደሩበት የሥራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመፃፍ ታሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናሻይል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ሰነድ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም በሥራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የሥራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ሥራውን በነፃ እንደሚሠራ ይወስዳል።

10. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝርና የጨረታ ማወዳደሪያ ስማቸው፣ ፊርማቸው አድራሻቸው ማስፈር ማህተም ማድረግ ኢንቭሎመት በማሸግ በት/ቤቱ ግቢ ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር G+1/008 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ት/ቤቱ ባስገነባቸው ግንባታዎችም ሆነ እድሳቶች ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይኖርባቸዋል።

12. አሸናፊ ተጫራች በሥራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (cost break down) ያቀርባል።

13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ድርጅት የሥራ ልምድ ማንኛውም በቴክኒክ የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሠሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠ አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።

14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር G+1/008 የሚከፈት ይሆናል።

15. ት/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 04 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አመ/ደ/ት/ቤት ከወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሰናዶ ት/ቤት ከፍ ብሎ ያዳም ዘውድ ሆቴል አጠገብ 100 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111119306/0904237685/0913436612

 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-30 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tibeb Edget Primary School
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T09:40:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders