Sewerage, drainage and sanitation

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በህንፃው ስር የሚገኘውን ቤዝመንት የቆሻሻ ፍሳሽ ለማጽዳት እንዲቻል የጽዳት አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 32/2018 በህንፃው ስር የሚገኘውን ቤዝመንት የቆሻሻ ፍሳሽ ለማጽዳት እንዲቻል የጽዳት አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 8፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ለበለጠ መረጃ፡- 0917012504/ 0116-47-95-78 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ:: ፋክስ 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-16
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-16 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Athletics Federation
  • Buyer address: ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Apr 05, 2026)
  • Posted at: 2026-04-06T11:08:40.000Z
← Back to all tenders