ቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/ኤ/ጤ/ጣ/02/2018 ዓ.ም

የጨረታ ቁጥር 02/2018

ለቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የሚገዛው ተዛማች አገልግሎት

.

የዕቃው አይነት

የሚያስይዙት ሲፒኦ በብር

1

የአይቲ እና የኤሌክትሮኒክስ ለኢንተርኔት ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎች

20,000.00

2

አላቂ የቢሮ እቃዎች

5,000.00

3

አላቂ የጽዳት እቃዎች

5,000.00

4

ፈርኒቸር

10,000.00

5

የሕትመት ሥራዎች

5,000.00

6

ልዩ ልዩ የጥገና መሣሪያዎች እና የጥገና ሥራዎች

5000.00

7

የሕክምና መሣሪያዎች እና ሬኤጀንቶች

10,000.00

8

የደንብ ልብስ

5,000.00

9

የፓርቲሽን ስራዎች

5,000.00

10

የጤና ባለሞያ እና ለአስተዳደር ሠራተኛ ዩኒፎርም የልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ

5,000.00

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣንጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾች የምስከር ወረቀት ያላቸው።

5. የአገር ውስጥ ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።

6. የአገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ./ CPO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቦሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ ኣለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት ገባ ብሎ ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ከርስቲያን አጠገብ 5ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቬሎፕ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በጤና ጣብያው ግዥ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አንደኛው (11ኛው) የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የሥራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን። ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ አይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት ናሙና የሚያስፈልጋቸው ሎቶች ማቅረብ አለባቸው። ከሰነዱ ጋር የተያያዘውን ስፔስፊኬሽን ላይ ማህተም በማድረግ መመለስ አለባቸው። ዘግይቶ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ /ሰዓት/ቀን አሳልፎ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

10. ጨረታው በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ቡድን ባዘጋጀው ኣዳራሽ 5ኛ ፎቅ ይከፈታል።

11. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስረከቢያ በማስያዝና ከግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።

12. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚወዳደሩ ለሚወዳደሩበት ሎት አምራች ስለመሆናቸው የሚገልጽ ከአደራጃቸው ወረዳ በበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ማምጣት አለበት።

13. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል።

14. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ከቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል

15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. የተሰረዘ የተደለዘ ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ይሰረዛል።

አድራሻ፡- ቦ/ከ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ ከመገናኛ ወደ ጎሮ በሚወስደው ጃክሮስ አለፍ ብለው አለማየሁ ሕንፃ ፊት ለፊት ባለው የኮብል ገባ በማለት ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ከርስቲያን አጠገብ 5ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን---ፎቅ ያነጋግሩን።

ስልክ ቁጥር፡- 011-639-5033

ሲፒኦ ሲዘጋጅ ፡- በኤረር ጤና ጣቢያ በሚል ይዘጋጅ።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው (11ኛው) የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው (11ኛው) የሥራ ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 7 የኤረር ጤና ጣቢያ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T12:03:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders