ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ሻሸመኔ ከተማ የሚገኝ ሕንጻ G+4 እና አዲስ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 /ግራር ሰፈር/ የሚገኝ ሕንጻ G+3 የውስጥ እድሳት ኮንስትራክሽን ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ሻሸመኔ እና አዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሁለት ሕንጻዎች የውስጥ እድሳት ኮንስትራክሽን ሥራ
ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 15/2025/26
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢማ ሻሸመኔ ከተማ የሚገኝ ሕንጻ G+4 እና አዲስ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 /ግራር ሰፈር/ የሚገኝ ሕንጻ G+3 የውስጥ እድሳት ኮንስትራክሽን ሥራ ሕጋዊና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡ዐዐ እስከ 6፡ዐዐ ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት የድርጅታቸውን የመስመር ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ አድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ያዘጋጁትን ሰነድ ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል።
- ጨረታው ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡15 ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይስረዛሉ።
- ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8097 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-04-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-22 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T12:20:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.