የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 007
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም ክልላዊ ፈተናን አስመልክቶ ሰርተፊኬት ፕሪንት ለማድረግ የሚያገለግል የፕሪንተር ቀለም Type Black Original Laser jet M611 Toner cartridge ቅልጥፍናና አቅም (Capacity)፡-አንዱ እስከ 10,000 ገጾች ፕሪንት ማድረግ አቅም ያለው ጥራት (Quality)፡- እውነተኛ ኦሪጅናል ምርት (1ኛ ደረጃ)(Genuine Product) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይንም መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፣
መስፈርት
1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ አስተማማኝ ዋስትና መስጠት የሚችል፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንዳንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 12,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና አብሮ ማቅረብ አለባቸው።
7. መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-771-06-88 መደወል ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ (ወራቤ)
Tender details
- Deadline: 2026-04-16
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-16 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Central Ethiopia Regional Government Education Bureau
- Bid bond: 12,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 06, 2026
- Posted at: 2026-04-07T08:51:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.