በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለውሃ ተቋማት ጥገና አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሮ መካኒካል መሣሪያዎች /ዕቃዎች/ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለውሃ ተቋማት ጥገና አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሮ መካኒካል መሣሪያዎች /ዕቃዎች/

በጨረታ መለያ ቁጥር፡- C/E/R/S/W/I/M/D/B/Rec. Capital Budjiet/001/18/ NCB በመደበኛ ካፒታል በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ስመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ላይ፤

1. የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈለ /Tax Clarence/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

2. በመስኩ /ዘርፉ/ ላይ የታደሰ የንግድ ፍቃድን ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

5. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

7. ለኤሌክትሮ መካኒካል መሣሪያዎች/ዕቃዎች, ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ብር 100000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከታወቀ ባንክ አስይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

8. ለኤሌክትሮ መካኒካል መሣሪያዎች ዕቃዎች ግዥ ከአምራች ድርጅት የተጻፈ ሕጋዊ የዕቃ ጥራት ማረጋገጫ ጋራንቲ የ/አንድ/ ዓመት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

9. የጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዕቃዎችን የሚያቀርበው በማ/ኢ/ክ/መ/የው/መ/ማ/ል/ቢሮ ወልቂጤ ከተማ በሚገኘው የቢሮው ንብረት ክፍል ማቅረብ የሚችል/የምትችል ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው መደበኛ አካውንት ቁጥር 1000573144628 ላይ ለሰነዱ መግዥ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጋችሁበትን እስሊፕ በመያዝ ወደ ቢሮው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ሥራ ክፍል በመሄድ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ እና ወደ ቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር- 22/23/ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን። ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል 1 /አንድ/ ኦርጅናል ዶክመንት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕመንት እንዲሁም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል 2 /ሁለት/ ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕመንት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 22/23/ በመውሰድ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታውን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በ15ተኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113659083/0926251559/ 0916393987 ደውሎ ማገኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ወልቂጤ ከተማ ወደ አዲስ አበባ መውጫ በሚወስደው የኣስፓልት መንገድ ጂኤንደፕ/G&P/ ከጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስተደቡብ አቅጣጫ 300 ሜትር ትንሽ ገባ ብሎ መሆኑን እንገልፃለን።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ /ወልቂጤ ኢትዮጵያ/


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ15ተኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-23 15:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በ15ተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: CERS Water Irrigation Mines Development Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T09:11:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders