የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ቡና ችግኝ ማፍያ ባለ 14 እና ባለ 20 ሚሜ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

ለ3ተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 12

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም /CAIM አገልግሎት የሚውል የአትክልትና ፍራፍሬ ቡና ችግኝ ማፍያ ባለ 14 እና ባለ 20 ሚሜ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆነን እንገልፃለን።

1, በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሉ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3. የግዥው መጠን ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ!

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕለስቲክ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃወች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Unconditonal Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የጨረታ/የመወዳዳሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 027 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ስነዱ ጋር አብረው መቅረብ አለባቸው፡፡

8.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።

 9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል። ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት። በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

12 በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-04-21 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Agriculture Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺ ብር/
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T10:56:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders