በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡_ 002/2018
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት
- ሎት 1 የህትመት ውጤቶች፣
- ሎት 2 ወንበር፣ ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣
- ሎት 3 ኮምፒውተር፣ ፕሪንተርና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣
- ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት 5 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት 7 የደንብ ልብስ እና
- ሎት 8 የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።
በዚሁ መሰረት፡-
1. ሎት 1 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 2 ወንበር፣ ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 3 ኮምፒውተር፣ ፕሪንተርና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ እና ሎት 8 የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለህትመት ውጤቶች ብር 5,000.00፣ ለቢሮ ዕቃዎች (ወንበር፣ ጠረጴዛ) ብር 5,000.00፣ ለኮምፒውተርና ፕሪንተር እና ሌሎች አገልግሎት ጥገና ግዥ ብር 5,000.00፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 10,000.00፣ ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 5,000.00፣ የደንብ ልብስ ብር 3,000.00፣ የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ብር 5,000.00፣ የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ብር 2000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ከ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30 እስከ 1፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል ከቅ/ጽ/ቤታችን የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው በመግለጽ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ምድር ላይ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን(የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ኦርጅናል እና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም።
10. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል።
11. ጨረታውን ለማባዛት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ለምታቀርቧቸው ናሙናዎች የምታመጡበት ዕቃዎች ጠንካራ እና በቀላሉ ሊቀደዱ የማይችሉ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- መገናኛ የካ ከ/ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 01 የግዥ ቡድን ክፍል ለበለጠ መረጃ
በሲ.ቁ. 09 11-68-45-54 እና 09 22-73-84 63 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-20 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka Sub City Land Development and Administration Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T08:41:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.