ሆፕ ኢንተርፕራይዝ (ERP: Accounting and Finance module) መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የእውቅና ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያስው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው። በመሆኑም የፋይናንስ ሥራ በተቀላጠፈ ሁኔታ ማከናወን እንዲያስችስን ሶፍትዌር ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ኢስር ፒ የአካውንቲንግ ሞጁል (ERP: Accounting and Finance module) መግዛት ፈልገናል።
ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈስጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ድርጅታችን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር C116 በአካል መጥታችሁ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09 74 17 66 00 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
1. ብቁ ተጫራቾች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር መክፈልና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- በመንግስት ያለባቸውን ግብር የመገበር ሃላፊነት እየተወጡ ያሉ፤
- ህጋዊ ውል ለመዋዋል የሚችሉ፤
- ያልከሰሩ፣ ክስ ላይ ያልሆኑ፤
- ጨረታ ለመሳተፍ የህግ መብት ያላቸዉ፤
2. የጨረታው አቀራረብና አከፋፈት
- የጨረታ ሰነድ መግዥያ ግዜ፡ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለ10 የስራ ቀናት (እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም)፤
- የጨረታ ማስገቢያ ቀን ገደብ፡- እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ቀኑ 6፡00 ሰዓት
- የጨረታ አከፋፈት፡- ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በ9:00 ተጫራቾች በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፤
3. ጨረታዎችን መገምገምና ማወዳደር
- አወዳዳሪ ኮሚቴው የገቡትን የጨረታ ሰነዶች ህጋዊ እና ቴክኒካል መስፈርቶችን ይገመግማል፣ ያወዳድራል፣
- ህጋዊ እና ቴክኒካል መስፈርቶችን ያሟሉ ብቻ ለፋይናንስ ውድድር ያቀርባል፣
- ህጋዊ እና ቴክኒካል መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሁም የተሻለ (ዝቅተኛ) ፋይናንስ ያቀረበ ብቻ ይመረጣል፣
- አጫራቹ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
4. ሙል አሰጣጥ
- የጨረታውን ውጤት በግልፅ አሸናፊውን ያሳውቃል፤
- ተቋማችን (ሆኢዩኮ) ከአሸናፊ ድርጀት ጋር የስምምነት ውሉን በህግ አግባብ ይፈፅማል፤
5. የአሸናፊ ድርጅቱ ግዴታዎች
- ምርቱን ለማቅረብ እና ዉል ለማሰር ማሸነፉን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 2 በሥራ ቀናት ዉስጥ በአካል ቀርቦ ዉል ይፈርማል፣
- ያቀረበው ሶፍተዌር እክል ሲገጥም የጥገና ድጋፍ መስጠት ችግሩን መፍታት ይኖርበታል፣
- ለሰራተኞች በሰትዌሩ አጠቃቀም ላይ በቂ ስልጠና ይሰጣል
- ላቀረበው ሶፍትዌር ቢያንስ የ2 ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ዉሎን በፈረመ በ2 ወር ዉስጥ ያሸነፈበትን ሶፍትዌር ባስገባው የጨረታ ሰነድ መሠረት ተግባራዊ ያደርጋል
6. የሚቀርጡ ሶፍተዌር ማሟላት ያለበት መስፈርቶች
Finance module that manages financial transactions, accounting processes, budgeting, financial reporting, and other financial activities within an organization.
Tender details
- Deadline: 2026-04-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-04-23 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hope Enterprises
- Buyer address: Addis AbabaEthiopia
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T12:39:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.