የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የወለል ምንጣፍ በናሙናው እና ቴክኒካል መስፈርቱ መሠረት በማቅረብ አንጥፎና ገጥሞ ማስረከብ፣ የመስኮት መጋረጃ ከመስቀያ ዘንግ፣ ቀለበት፣ ማሰርያ ገመድ እና ከነ መያያዣው ጋር በናሙናው እና ቴክኒካል መስፈርቱ መሠረት በማቅረብ ገጥሞ እና ሰቅሎ ማስረከብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን u208 በጀት Sf ለመግዛት ላቀደው እና ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አገልግሎቱ ዓይነት

መለኪያ

 

ብዛት

 

የሚገጠምበት ቦታ

ሎት

 

የጨረታ ማስከበርያ

1

የወለል ምንጣፍ በናሙናው እና ቴክኒካል መስፈርቱ መሠረት በማቅረብ አንጥፎና ገጥሞ ማስረከብ

ካሬ

280

የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሃዋሳ

1

11000

 

2

የመስኮት መጋረጃ ከመስቀያ ዘንግ፣ ቀለበት፣ ማሰርያ ገመድ እና ከነ መያያዣው ጋር በናሙናው እና ቴክኒካል መስፈርቱ መሠረት በማቅረብ ገጥሞ እና ሰቅሎ ማስረከብ

ካሬ

85

የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሃዋሳ

2

4000

1. በ2018 ዓ/ም ፊቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN N..) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።

2. ምንጣፍ እና መጋረጃ በማቅረብ ማንጠፍ እና መግጠም የሚችሉ።

3. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በየሎቱ በተቀመጠው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና BANK GAURANTEE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዢ ፋይናንስ ን/አ/ዳሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

5. የጨረታው ሰንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ከተጨማሪ አንድ ኮፒ ሰነድ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዢ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የዕቃዎችን ብዛት መጠን እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመደበኛ የጨረታ ሰነድ ውስጥ ክፍል 4 ላይ በዝርዝር ያገኛሉ።

7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ይከፈታል፣ ይሁንና የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡

8. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይከናወናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462124639 መደወል ይችላሉ።  

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-21 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T08:59:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders