በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በስሩ ለሚያስተዳድራቸው መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር እቃ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በስሩ ለሚያስተዳድራቸው መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

ሎት 1 የፈርኒቸር እቃ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎችን ይጋብዛል።

1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1፡- የፈርኒቸር እቃ 40,500 (አርባ ሺ አምስት መቶ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ። በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የግዥው አይነትና ሎት በመፃፍ በገንዳውሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

4. የጨረታ ሰነዱን ከገ/ውኃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ሁኖ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ። ጨረታዉ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዝውኃ ከተማ አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በግልፅ ይከፈታል

6. ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

7. አሽናፊው ድርጅት ንብረቱን በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የሌለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 05 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።

10. ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም በተጨማሪም የእቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

11. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካለ በጽ/ቤቱ የውስጥ ሰሌዳ የምናሳውቅ መሆኑ

12. የአብክመ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1/2003 እና በተጨማሪ በቢሮው የወጡ የመመሪያ ማሻሻያዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል

13. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

14. ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0583310566 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

 በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደውሃ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-04-30 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: West Gondar Zone Gendawuha Administration FEDB
  • Bid bond: 40,500.00 (አርባ ሺ አምስት መቶ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T09:15:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders