የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የፕላስቲክ ብርጭቆ (Plastic Glass Tumbler) አምራች ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሶሥት (3) አመት በሚቆይ የኮንትራት ስምምነት ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T608
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ ላስቲክ ብርጭቆ (Plastic Glass Tumbler) አምራች ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሶሥት (3) አመት በሚቆይ የኮንትራት ስምምነት ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ በዘርፉ ከኢትዮጵያ የጥራት ና ደረጃዎች የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፣ የተፈላጊውን ምርት ናሙና ማቅረብ የሚችል ፣ ሁለት (2) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277( -99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T608 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 300,000.00 / (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርበታል:: ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ከባንክ የሚቀርብ ውስንነት ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም:: አሽናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾቾ ያስያዙትን የጨረታ ማስከብሪያ ወዲያውኑ ተመላሸ ይሆናለ።
4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ (ሲ.ፒ.ኦ) ጨምረው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:15 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ወ/ት ቅድስት ማሞ
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4258
ኢ-ሜይል: KidistMm@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-05-04 15:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Buyer TIN: 0000028498
- Bid bond: 300,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:45:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.