የካቲት23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮምፒዩተር እና ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ከአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋል።

ሎት 1  ኮምፒዩተር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 159600.00
ሎት 2  ጀነሬተር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80000.00

በዚህ መሰረት ከዚች በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ የሚያቀርብ - የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር ያላቸው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ብር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በፅህፈት ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  •  ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ማንኛውም ሳምጥል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመግኘት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  •  ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ3፡30 ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ታሽጎ በ4፡00 አራት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ። ሙሉ ሰነዱን ያላስገባ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
  •  የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ 10% ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  • ተጫራቾች በመንግስት ግዥ ዌብሳይት ላይ ድርጅታችሁ ተመዝግቦ መገኘት አለበት።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112768120/0112303241/0112303054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ - አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደመሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት

የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-23
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-23 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yekatit 23 General Secondary School
  • Buyer address: አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከአውቶቡስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 11, 2026
  • Posted at: 2026-04-11T08:58:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders