ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተቋሙ አገልግሎት የሚዉል CCTV Surveillance System for Warehouse በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/29/18
ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተቋሙ አገልግሎት የሚዉል CCTV Surveillance System for warehouse በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ማግኘት ይቻላል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-156 9992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-28 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: 100,000 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T08:04:39.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.