በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ጤና ጣቢያ የተለያዩ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማግኘት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3ጤና ጣቢያ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ ይመልከቱ
- ሎት 1 የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች እና እቃዎች ግዥ እና የላብራቶሪ መመርመሪያ ማሸኖች ጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። እና
- ሎት2 የመፀዳጃ ቤት ታንከር ቦቲ መኪና ያላቸውን በሙያው የተሰጠ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን በጨረታ አወዳድሮ ማስመጠጥ /ማስነሳት ይፈልጋል፡፡ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር (ሁለት ሺ) ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣ ለመፀዳጃ ቤት ብቻ።
ሎት 1 ሪኤጀንት እና ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ብር (ሰላሳ ሺ) ብር በመንግሥት ከሚመለከተው አካል ፍቃድ የተሰጠው አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዥና ምግብ መድኃኒት ባለሥልጣን ኤጄንሲ የምስክር ወረቀት ያለው።
- የጨረታ ቁጥር 003 ፣ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ምግብ መድኃኒት ባለሥልጣን ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ ቲንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ) ሪኤጄንቶች እና እቃዎች 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ግራር ወፍጮ ሀናን ዳቦ ቤት መውጫ መንገድ ላይ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 47 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛትይቻላል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጨማሪም ሪኤጀንቶች ቴከኒካል እስፔስፍኬሸን ላይ በተቀመጠው እስታንዳርድ መሰረት ማቅረብአለባቸው።
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
- ገዥው በአካል የሚገዛውን ሪኤጀንት እስከ 20% ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ በማሸግና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከዚህ በላይ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ቁጥር 52 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ወይም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
- አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን በኋላ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሠርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ታሸጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 52 ውስጥ ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያው አየር ጤናን አልፎ በተለምዶ ግራር ወፍጮ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አለፍ ብሎ ሀናን ዳቦ ቤት መውጫ መንገድ ላይ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 20 80 90 99 ይደውሉ።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-24 10:30
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኮልፊ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T09:02:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.