የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮምፒተር እና ጀኔሬተር እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ለ2018  ዓ.ም በጀት አመት ቁጥር 002 /2018 አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።

.

የእቃው አይነት

የሚያሲዘው የብር መጠን እና ፐርሰንት

1

ኮምፒተር

1

159,600.00   2. ፐርሰንት

2

ጀኔሬተር

2

80,000.00    2. ፐርሰንት

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል።

  1. የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺ/ ብር በላይ የሆነ ግዢና አገልግሎት ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝግቢ የሆኑና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ተጫራቾች በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ የስራ ፍቃድ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው በዌብሳይት የተመዘገቡ መወዳደር ይችላሉ። እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በተፈቀደላቸው ዘርፍ ላይ ብቻ ስለሆነ ሰነድ በነጻ የሚሰጣቸው የተፈቀደላቸውን ዘርፍ ፍቃድ ኮፒ ማምጣት ሲችሉ ብቻ ነው።
  2. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነ መጓጓዣው በሚያቀርበው የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውሰጥ አካቶ ማቅረብ አለበት ነጠላ ዋጋውን ከነቫቱ ማስቀመጥ የሚቻለው የጨረታ ሰነዱላይ ባለው ቦታ ብቻ ሲሆን ከአንድ በላይ ዋጋ የሚያቀርቡበት ካለ ግን ኮፒ በማድረግ ሁለተኛ ገጽላይ ጽፈው አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ። እንዲሁም ዋጋ ከነቫቱ አስቀምጡ ተብሎ በተጻፈው መሰረት የተቀመጠውን ዋጋ ከነቫቱ እንደሆነ ነው የምንወስደው። መክንያቱም የአንዱ ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ ስለተጠየቀ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(CPO)ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶ መሰረት በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይንም የተወዳደሩበትን የጠቅላላ ዋጋ 0.5-2 ፐርሰንት ድረስ ከላይ በየሎቱ በተቀመጥው የብርና የፐርሰንት መጠን በአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳደሪዎች ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ካደራጃቸው ተቋም የጨረታ ማስከበሪያ ወይንም ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ ህጋዊ የሆነ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
  4. እንዲሁም ተጫራቾች ጨረታውን እንዳሸነፉ ከተገለጸላቸው በኋላ በሚጠቀሰው የገንዘብ መጠን ልክ አጠቃላይ የዋጋውን 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማምጣትና መዋዋል ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም አሸናፊዎች ከተገለጸላቸው በኋላ እቃው ጠፍቷል እቃው መግባት አይችልም ወይንም ገና ሊመረት ነው ወይንም ዋጋ ስለጨመረ እና እንዲሁም ተመሳሳይ ያልሆነ እቃ ለመስገባት መሞከር ተጠያቂነትን ያስከትላል በተጨማሪም አነስተኛና ጥቃቅን ተጫራች ከሆኑ
  5. ላደራጃቸው ወይንም ዋስትና በአድራሻችን ጽፎ ደብዳቤ ለላከው ተቋም አስፈላጊውን የተጠያቂነት ፎርም ሞልተን እንደምናሳውቀው እና ለሚመለከተው አካል የም ናስተላልፍ መሆኑን አውቀው ሁሉም ተጫራቾች ከወዲሁ የጨረታውን ጥራት ጠብቀው መወዳደር ይጠበቅባቸዋል ።
  6. ጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በመቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  7.  ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳንምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ማንኛውም ሳምፕል የሚያስገባ ተወዳዳሪ በአስራ አንደኛው ቀን ቢያመጣ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ አውቆ ከመከፈቱ ከ3ቀን በፊት ማስገባት እንዳለበት እያሳወቅን ሳንምፕል ለማይቀርብባቸው እቃዎች ት/ቤቱ  በስፌስፊኬሽኑ መሰረት የተጠየቁ እቃችዎን መወዳደርና ማቅረብ ይቻላል ሌላው በመዝጊያና በመከፈቻ ቀን የሚመጡ ሳምፕሎችን የማንቀበል መሆኑን በድጋሚ እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ናሙና ና ማቅረብ አስቸጋሪ ለሆኑ ወይንም ከብደት ላላቸው እንደ ጄነሬተር ያሉ  እቃዎች የሚወዳደሩበትን እቃ እስፔስፊኬሽን ወይንም ፎቶ ማቅረብ ይችላሉነገር ግን ኮምፒተር ተወዳዳሪዎች ሙሉ ኮምፒተሩ በአካል መቅረብ አለበት ኮምፒተሩ ካልቀረበ በፎቶ እና በስፌስፊኬሽን ብቻ መወዳደር አይችሉም ። እንዲሁም በተጨማሪ የንግድ ቦታድረስ በመሄድ የሚታይ ይሆናል።
  8. ለውድድር ያስገቡትን ናሙና ጨረታውእደተጠናቀቀ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሳይወስዱ ግን እስከ 6 ወር ድረስ ከቆዩ ላስገቡት ናሙና እና ማንኛውንም ነገር የማንጠየቅ እና ሃላፊነት መውሰድ የማንችል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምክንያቱም የአገልግሎትቀኑ ሊያልፍና ሊበላሽ ሊቀደድ ሊሰበር ስለሚችል ነው።
  9. ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን የምዝገባ ፍቃድ ቫት ቲን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ንግድ ፍቃድ ያደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰነድ ሙሉ የዋጋ ዝርዝራቸውን ጭምር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የሁሉንም ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ለብቻ ፖስታ ቴክኒካ ለብቻ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይመለሳል። ይህ ማስታቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተፈቀደው ዋናና ኮፒ ሰነዶች ቀንሶ ማስገባት አይፈቀድም፡፡ እንዲሁም ዋናላይ የሚገቡ ሰነዶች ኮፒላይ በስህተት ቢገባም ከኮፒ ውስጥ ሰነድ ወቶ እንደ ኦርጅናል ተከፍቶ ሊታይለት አይቻልም ሊወዳደርበትም የማይችል መሆኑን እንገልጻለን። በሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ወይም ስርዝ ድልዝ መረጃ ተቀባይነት የለውም።
  10. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3.00 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቾች ጨረታ ላይ መገኘት ካልቻሉ ህጋዊ ወኪሎቻቸውን መላክ ይችላሉ። ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስፈርቱን ካሟሉ ባይገኙም ያልተገኙትም ተጫራቾች ፖስታ ጭምር ይከፈታል፡፡ የጨረታ አከፋፈት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዝግ የሆኑ ቀናቶች ከገጠመ በሚቀጥለው ከፍት የሰራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ወዲያውኑ በመቅረብ እቃውን ከማስገባቱ በፊት የአጠቃለይ ያሸነፈባቸውን እቃ ዋጋ አስር ፐርሰንት ብር (CPO) ከላይ በተጠቀሰው ስም ከባንክ በማሰራት ውል በመዋዋል ያሸነፉባቸውን እቃዎች ግዢ ፈጻሚው መስሪያቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች እንዳሸነፉ ከተገለጸላቸው በኋላ እቃ እጄ ላይ የለም ቀጠሮ ይሰጠን በሚል የተለያዩ ምክንያቶችን ማቅረብ አይፈቀድም ምክንያቱም እጅ ላይ ባለ እቃ ነው መወዳደር የሚችሉት ይህ ሳይሆን ቢቀርና ማሸነፋችሁ ከተገለጸ በኋላ እቃ ጠፍቷል ጊዜ ስጡኝ የሚል ጥያቄ እናስተናግድም። ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እንጠይቃለን፡፡ ሌላው ደግሞ ማንኛውንም እቃ ከ9፡00 ሰዓት በኋላ ጭነው ቢመጡ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ምክንያቱም ጥራት ኮሚቴ አይቶ ፈትሾ ስለሚያስገባ ሰዓት ስለሚያጥር ነው።
  11. ት/ምርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ወይንም ከ20 ፐርሰንት በላይ የመቀነስ መበቱ የተጠበቀ ነው ።

አድራሻ ለዲስ ከተማ የክፍለሃገር አውቶብስ ተራ ለጠገብ የሚገኘው አዲስ

ከተማ አጠቃሳይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112763811/15/17

በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ  ት/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-04-24 09:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Education Office Addis Ketema Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T11:54:20.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders