Environmental and social impact assessment

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ 5 የክልል ኤርፖርቶች ውስጥ የዱር እንስሳት አደጋ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና ጥናት (ECOLOGICAL INVESTIGATION AND ANALYSIS OF WILDLIFE HAZARD AT ETHIOPIAN AIRPORTS) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T 611

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ 5 የክልል ኤርፖርቶች ውስጥ የዱር እንስሳት አደጋ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና ጥናት (ECOLOGICAL INVESTIGATION AND ANALYSIS OF WILDLIFE HAZARD AT ETHIOPIAN AIRPORTS) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና አጥኚዎችና አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች በአገር ውስጥ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ተመዝግበው የምርመራ እና ትንተና አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው እና በዘርፉ ለመስራት ለ2018 ዓ.ም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T 611 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

5. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አንድ መቶ ሰባ ሺህ ብር (170,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

6. አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሀሙስ ሚያዝያ 22,208 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028

ኢ-ሜይል: [email protected]

አየር መንገዱ የተሻስ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-04-30 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 170,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Apr 13, 2026)
  • Posted at: 2026-04-14T12:58:28.000Z
← Back to all tenders