የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለአቶ እንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባለበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም

የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ

የድርድሩ መነሻ ዋጋ

ደረጃ

 

ድርድር የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት

 

1

ኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ፣ አዋሽ ብሾላ ቀበሌ ውስጥ 1 ሄከታር ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የእንሰሳ (በግ/ፍያል) ማረጃ ማሽኖች፣ ጀኔሬተር እና አንድ ባለ ማቀዝቀዣ ዩዲ ኒሳን ተሸከርካሪ

44,999,333.61

 

1ኛ

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት መ/ቤት ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

2

እንዳልካቸው ንጋቱ

በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ፣ ጆጎ ጉዴዶ ቀበሌ ውስጥ 6000 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የወተት ማቀነባበሪያ መሽኖች እና 6 (ስድስት) ተሽከርካሪዎች

46,286,021.48

 

1ኛ

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት መ/ቤት ግንቦት 07 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

 

ማሳሰቢያ

1. ተደራዳሪዎች የድርድሩን መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ።

2. ተደራዳሪዎች የሚገዙትን ንብረት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፤ ስምና አድራሻ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተ.ቁ 1 እስከ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ለተ.ቁ 2 እስከ ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

3. ተደራዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪክት መውሰድ ይችላሉ።

4. ንብረቱን በብድር መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ የባንኩን የብድር መስፈርት ማሟላትና ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ፣ ስለ ቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ሁኔታ፣ ለቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ከሚገዙት ንብረት በተጨማሪ የሚያቀርቡት የመያዣ ዐይነት፣ግምትና የሚገኝበት ቦታ በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል።

5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተደራዳሪዎች ያስያዙትን ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረጋል።

6. የጉምሩክ ቀረጥና ታከስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል።

7. የድርድሩ አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።

8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ድርድሩን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-6687 ላይ መደወል ይቻላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-05-15 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 10%
  • Published: Apr 14, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T13:40:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders