ፀደይ ባንክ አ.ማ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ሞላ ታከለ እና ለወ/ሮ አዲሴ ደመላሽ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በአማራ ክልል በአዊ ዞን በእንጅባራ ከተማ በካርታ ቁጥር 57/2007 በአዋሳኝ በምሥራቅ ጌታቸው የማታ፣ በምዕራብ ይስማው አለማየሁ፣ በሰሜንና በደቡብ መንገድ የሚያዋስናውን የተበዳሪዎች ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በመነሻ ብር 14,373,163.56 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ
|
የተበዳሪ ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
ጨረታ የሚካሄድበት |
ጨረታ የወጣው |
|||||
|
ለጨረታ የቀረበ ንብረት |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የካርታ ቁጥር/ የይዞታ መለያ ቁጥር |
የቦታው ስፋት በካ/ሜ
|
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
||||||
|
1 |
ሞላ ታከለ እና አዲሴ ደመላሽ |
ሞላ ታከለ እና አዲሴ ደመላሽ |
እንጅባራ |
የምግብ ዘይት ፋብሪካ |
እንጅባራ |
57/2007 |
1500 ካ.ሜ
|
14,373,163.56
|
06-09-2018
|
ከ4፡00-6፡00 |
በዲስትሪክት 3ኛ አደራሽ
|
ለመጀመሪያ ጊዜ
|
የሐራጁ ደንቦች
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1⁄4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንናቱን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ቃላ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ።
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ፣ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የስበሳባ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ዳቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፈል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 እና 09 10 30 20 03 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፀደይ ባንክ አ/ማ እንጅባራ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-05-14
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-05-14 12:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-15T11:22:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.