የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ ሸቀጦችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ (ቁጥር 005/2018)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ፓስታና ማካሮኒ CES 1055፡20222.
- ፈሳሽ የሱፍ ዘይት (CES17:) and labeling CES 73
- ከሸንኮራ አገዳ የተመረተ ስኳር ICUMSA 45 (SUGAR CANE)
- አንደኛ ደረጃ የበለፀገ የዳቦ ዱቄት CES 309፡2022
- የቆርቆሮ እና ግድግዳ ሚስማር
- የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 21:2024)
- የተለያየ መጠን ያላቸው ፎጣዎች
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ለስኳር እና ፈሳሽ የሱፍ ዘይት አምራች ወይም አስመጭና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ምርቶች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ዋና ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርቴፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
3. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።
6. ጨረታው በተመሳሳይ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 011-128-15-29
www.eiide.com.et.com.et
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-28 10:10
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopia's Industrial Inputs Development Enterprise
- Buyer address: በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሐንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ|ቤት)።
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 15, 2026
- Posted at: 2026-04-15T11:36:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.