ቢፍቱ ሪዞርት (Biftu Resort) በሱሉልታ ከተማ ለሚገኘው የሪዞርት ማስፋፊያ ሥራ አዲስ ለሚከፈቱ ካፌ፣ ባር፣ ሬስቶራንት እና ጂም (Gym) የሚሆኑ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቢፍቱ ሪዞርት (Biftu Resort) በሱሉልታ ከተማ ለሚገኘው የሪዞርት ማስፋፊያ ሥራ አዲስ ለሚከፈቱ ካፌ፣ ባር፣ ሬስቶራንት እና ጂም (Gym) የሚሆኑ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

የጨረታው ዘርፎች፦

1. የካፌ እና የባር መሣሪያዎች (የኤስፕሬሶ ማሽን፣ መፍጫ ወዘተ)

2. የሬስቶራንት የገበታ ዕቃዎች (ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች ወዘተ)

3. የወጥ ቤት ማብሰያ እና ማዘጋጃ መሣሪያዎች (ድስቶች፣ ቢላዎች ወዘተ)

4. የጂም መሣሪያዎች (ትሬድሚል፣ ብስክሌት ወዘተ)

5. ጥገናና እድሳት (Maintenance & Finishing)

የግድግዳና ወለል ጥገና፦ ነባር የተሰነጠቁ ግድግዳዎችን፣ ጣሪያን መጠገን እና የወለል ንጣፎችን (Tiles/Terrazzo) ማስተካከል።

የውሃና ኤሌክትሪክ ጥገና፦ የቧንቧ መስመሮች ፍሳሽ ፍተሻና ጥገና፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችና የመብራት ፊቲንግ መቀየር።

የቀለም ቅብ ስራ፦ የውስጥ (lnterior) እና የውጭ (Exterior) ግድግዳዎች ጥራት ባለው ዘመናዊ ቀለም መቀባት።

የአሉሚኒየም ስራ፦ የበርና መስኮት ጥገና ወይም አዲስ መቀየር።

6. የቤትና የቢሮ ዕቃዎች አቅርቦት (Furniture)

መኝታ ቤት፦ የኪንግ ሳይዝ (King size) እና ትዊን (Twin) አልጋዎች ከነ ፍራሻቸው (Orthopedic)፣ ማረፊያ ሶፋ።

ተጓዳኝ ዕቃዎች፦ የጎን ጠረጴዛዎች (Nightstands)፣ የልብስ ቁምሳጥን (Wardrobe) እና የመዋቢያ ጠረጴዛ ከነ መስታወቱ።

ለካፌ መቀመጫ፦ የቡና ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች እና የሶፋ ሴቶች።

7. የኤሌክትሮኒክስና የጨርቃጨርቅ አቅርቦት

ኤሌክትሮኒክስ፦ ስማርት ቲቪ (Smart TV)፣ ሚኒ ባር ፍሪጅ (Mini Fridge)፣ የውሃ ማፍያ (Kettle) ፣።

ጨርቃጨርቅ፦ አንሶላዎች፣ ብርድ ልብስ ፣ ትራስና መጋረጃዎች (Blackout curtains)፣ ፎጣ ፣ የመታጠቢያ ቤት የእግር ምንጣፍ ።

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የTIN እና የVAT ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው መሣሪያዎች ቢያንስ የ 1 ዓመት ዋስትና (Warranty) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤

የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 10,000.00 ማቅረብ የሚችሉ፤

የሰነድ አቀራረብ እና መመሪያ፦

ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000647131868 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ሜከሲኮ ከአፍሪካ ህብረት ከፍ ብሎ Ethio engineering group ፊት ለፊት ኤግል ፕላዛ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 005።

ለተጨማሪ መረጃ፦ 09 13 26 77 76 / 09 35 02 46 22 / 09 89 10 82 20

ማሳሰቢያ፦ ሪዞርቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቢፍቱ ሪዞርት (Biftu Resort)


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-27 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Biftu Resort
  • Buyer address: አዲስ አበባ ሜከሲኮ ከአፍሪካ ህብረት ከፍ ብሎ Ethio engineering group ፊት ለፊት ኤግል ፕላዛ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 005
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 16, 2026
  • Posted at: 2026-04-16T08:03:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders