የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ እና በአዳማ ከተማ የተለያየ የኮከብነት ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል

Description

 ሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢ.ሰ.መ.ኮ.ብ /ግ/ጨ /ፋ/ አ/ስ/ክ/06/18/2026

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ መሰረት ነጻ ፌዴራላዊ መንግሥት አካል ሆኖ የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት መከበርና ጥበቃ የሚሰራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ሲሆን ለተለያዩ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች የሚሆን የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ እና በአዳማ ከተማ የተለያየ የኮከብነት ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ፤

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብርም ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ታክስ ከሊራንስ ማቅረብ ማያያዝ አለባቸው። እንዲሁም ሆቴሎቹ የተሰጣቸውን የኮከብነት ደረጃ የሚገልጽ ሰርተፍኬት ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር

ከዚህ በፊት ለሰሯቸው ሥራዎች እውቅና የተሰጠበት ሰርተፊኬት ወይም የምስጋና ደብዳቤ እና ሌሎች ዝርዝር መገምገሚያ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

ኮሚሽኑ የሚፈልገው የአገልግሎት ዓይነት ለባለ 5፣ 4 እና 3 ኮከብ ደረጃ ሆቴሎች

ሀ. የመሰብሰቢያ አዳራሽ (እንደየሰው ብዛት ተለዋዋጭነት ያለው)

ሊ የመኝታ አገልግሎት

ሐ. የእራት መስተንግዶ አገልግሎት

መ. የምሳ መስተንግዶ አገልግሎት

ሠ. ሁለት ጊዜ የሚቀርብ የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት 1/2 ሊትር የማዕድን ውኃን ጨምሮ

ረ. አንድ ጊዜ የሚቀርብ የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት 1/2 ሊትር የማዕድን ውኃን ጨምሮ

*የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ብር 10,000.00 (ብር አስር ሺህ) ለብቻው በታሸገ ፖስታ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ጨረታው ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ማለትም ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  • ኮሚሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኮሚሽኑ 3ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል መውሰድ ይችላሉ።

አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ፊት ለፊት ሐያት ሬጀንሲ አጠገብ ሰንሻይን ህንጻ ቁጥር 5

ስልክ ቁጥር +251 115187030

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-04-30 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Human Rights Commission
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Published: Apr 17, 2026
  • Posted at: 2026-04-17T07:51:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders