ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. የጥበቃ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጥበቃ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 17-2025/26
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ የጥበቃ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራና አሰሪን ለማገናኘት የተሰጠ ለ2018 ዓ.ም ሥራ ፈቃድ ያለውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት የድርጅታቸውን የመስመር ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ አድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ : አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ይሆናል። ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተቱ ሆነዉ ማንኛውንም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 3 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ያዘጋጁትን ሰነድ ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል።
8. ጨረታው ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡15 ላይ ይከፈታል:: ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይሰረዛሉ:: ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 12 04 ወይም 011 531 80 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-06 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T12:14:15.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.