አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኘው ሪከቨሪ የጥበቃ እና የፅዳትና ተላላኪ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚገኙ ቅርንጫፎች የፅዳት እና ተላላኪ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጥበቃ እና ፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ
ቁ07/25/26
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኘው ሪከቨሪ የጥበቃ እና የፅዳትና ተላላኪ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለሚገኙ ቅርንጫፎች የፅዳት እና ተላላኪ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- በመሆኑም ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ በዘርፉ የተመዘገበና ወቅታዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- ስራና ሠራተኛን ለማገናኘት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- በተጨማሪም የታደሰ እና በዘርፉ የተመዘገበ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል ግብር መክፈያ መለያ (TIN) ሰርተፊኬት ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ክሊራንስ እና ጨረታ ለመጫረት የሚያችል ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ስለሆነም የተጠየቀውን አገልግሎት ማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከ ከአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ድረስ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
የመጫረቻ ሰነዱን በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በማለት አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት (4ተኛ ፎቅ) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ጨረታው ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት 4፡30 በኩባንያው ግዥ ኮሚቴ የሚከፈት ይሆናል።
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀነው።
አድራሻ፡- አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)ኃይሌ ገ/ስላሴ ጐዳና አንበሳ ኢንሹራንስ ህንፃ
ስልክ፡- 011 618-7000/011-662 8135
Tender details
- Deadline: 2026-04-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-25 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lion Insurance Company S.C.
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T12:18:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.