Edible oils, sugar and salt
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ (ቁጥር 005/2018)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
1. ፓስታና ማካሮኒ CES 1055፡20222.
2. ፈሳሽ የሱፍ ዘይት (CES17) and labeling CES 73
3. ከሸንኮራ አገዳ የተመረተ ስኳር ICUMSA 45 (SUGAR CANE)
4. አንደኛ ደረጃ የበለፀገ የዳቦ ዱቄት CES 309-2022
5. የቆርቆሮ እና ግድግዳ ሚስማር
6. የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 21:2024)
7. የተለያየ መጠን ያላቸው ፎጣዎች
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ለስኳር እና ፈሳሽ የሱፍ ዘይት አምራች ወይም አስመጭና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ምርቶች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ዋና ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርቴፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድኮፒ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ::
- ጨረታው በተመሳሳይ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 011-128-15-29
www.eiide.com.et.com.et
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-04-28 10:10
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise
- Buyer address: ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Reporter (Apr 19, 2026)
- Posted at: 2026-04-20T14:49:58.000Z