የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ የባለ አራት ኮከብ የሆቴል አገልግሎት ለአንድ ዓመት የሚቆይ በማዕቀፍ ግዥ የዉል ስምምነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የባለ አራት ኮከብ የሆቴል አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/15/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ የባለ አራት ኮከብ የሆቴል አገልግሎት ለአንድ ዓመት የሚቆይ በማዕቀፍ ግዥ የዉል ስምምነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እናበመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስክ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-+251 11 515 3468
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-04-30 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian National Election Board
- Buyer address: ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 21, 2026
- Posted at: 2026-04-21T11:07:57.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.