የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግሥት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ለቪዲኦ ኮንፈረንስ ክፍል (VCroom) የሚሆኑ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግሥት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ለቪዲኦ ኮንፈረንስ ክፍል (VCroom) የሚሆኑ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በኤሌክትሮኒክስ ንግድ ወይም በቴክኖሎጂ ግብዓት ቁሳቁስ አቅርቦት ሥራና ተዛማጅ ሥራ የተሰማራችሁ

በሚከተሉት መመዘኛዎች መሠረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡-

1. ተፈላጊ መመዘኛዎች

  • የሥራ ዘርፉ፡- በኤሌክትሮኒክስ ወይም በቴክኖሎጂ ግብዓት/ቁሳቁስ አቅርቦት እና ተዛማጅ ሥራ፡፡
  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN) ያለው።
  • የቅርብ ጊዜ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) እና በመንግሥት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።

2 የሥራው ዝርዝር ይዘት

  • የሥራው ቦታ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ክልል መንግሥት ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ፡፡
  • የሥራው ዓይነት፡- የቴክኖሎጂ ግብዓት/ቁሳቁስ ማቅረብና እስከ ቴፒ ከተማ በሚገኘው የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ማድረስ፡፡

3. የጨረታ ሰነድ አገዛዝ እና አቀራረብ

ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በቢሮ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000705389137 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በቢሮአችን በሚገኘው የግዥ ፋይናንስ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) መጠን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የጨረታ ሰነዱ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ) በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል።

4. ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ጊዜ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን በ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል። (22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል)።

ማሳሰቢያ፡-ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ፡

ስlክ፡-+251912932500

አድራሻ፡ ቴፒ

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግሥት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-12 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 21, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T11:49:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders