ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ሀጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

★ Featured

Description

ቀን ፡ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም.   ለህንጻ እድሳት ሥራ የቀረበ ጨረታ   ለ፡ ---------------------------   ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ሀጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ደረጃ ሰባት እና በላይ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ፈቃድ እና የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡   ለዚህ ሥራ የተጠሩት ተጋባዥ ተጫራቾች፤

  1. የሥራ ልምዳቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ እንዲያቀርቡ ይፈለጋል፡፡
  2. ለዘመኑ የታደሰ የንግድና ሥራ ፍቃድ ምዝገባ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡

ከዚህ ደብዳቤ ጋር በቀረበው የሥራ ዝርዝር መሰረት ለቀረቡት ሥራዎች የማቴሪያል እና የእጅ በአንድነት አካቶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ከማህበሩ ጽ/ቤት ዘውትር በሥራ ሰዓት (ከጧቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡30) ከሚያዚያ 19 እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10000.00 (አስር ሺ) በሲፒኦ ወይም በቢድ ቦንድ መልክ አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ጽ/ቤት በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡   ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከማቅረባቸው በፊት ህንጻዎቹ ያሉበትን ሁኔታ በአካል በመቅረብ እንዲጎበኙ ይመከራል፡፡ ተጫራቾች ለቴክኒክ ምዘና የሚያስፈልገውን የተሟላ ሰነድ በተለይም ከዚህ ቀደም ያከናወኑትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሚገልጹ ሰነዶችን ከህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሰነዶች ጋር አያይዘው ቴክኒካል ፕሮፖሳል ኤንቨሎፕ ውስጥ ከጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጋር በኤንቨሎፕ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የዋጋ ማቅረቢያው (ፋይናንሻል ፕሮፖሳል) በሌላ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡   አሰሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡   ከሰላምታ ጋር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid opening: 2026-05-06 16:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-22T12:15:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders