አንድ ሚሊዮን ብርቱ (One Million Birtu (OMB) የዲዛይን እና ግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት ይፈልጋል
Description
የዲዛይን እና ግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
1. የሥራው ዓላማ
አንድ ሚሊዮን ብርቱ (One Million Birtu (OMB) ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዋና ዓላማውም እስከ 2030 ዓ.ም የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ማሻሻል ነው። ድርጅቱ ከዘላቂ የልማት ግብ 7 (SDG 7) ጋር በተጣጣመ መልኩ ንጹህ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሁሉን አቀፍ እና ሰፊ ተደራሽነት ያላቸውን መፍትሄዎች በማቅረብ ላይ ያተኩራል።
ይህንንም ለማሳካት በጠምባሮ ልዩ ዞን፣ ሙዱላ ወረዳ ለሚገነባ ኮንፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት (Comprehensive Health Post) ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ስራዎች መስፈርቱን ለሚያሟሉ ብቃት ያላቸውን አማካሪዎች (ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ሙሉ የአርክቴክቸር እና የምህንድስና ዲዛይን አገልግሎቶች
- የዋጋ ዝርዝር (BoQs) እና የቴክኒክ ሰነዶች ዝግጅት
- ግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር
ግንባታው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስፈርትን የጠበቀ እና Compressed Earth Block (CEB) ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ይሆናል። የስራው ቆይታ ጊዜ ለዲዛይን እና የቅድመ ግንባታ ምዕራፍ 5 ሳምንታት ፤ ለግንባታ ቁጥጥር 6 ወራት ነው።
2. ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት አማካሪ ወይም ድርጅት።
- ቢያንስ 3 ዓመት ተዛማጅ የሥራ ልምድ፡
- ተመራጭ ሁኔታዎች፡ በCEB ቴክኖሎጂ፣ በጤና ተቋማት ግንባታ እና በገጠር አካባቢዎች የመሥራት ልምድ ያልው ያላት።
7. የማመልከቻ ዝርዝሮች
- መስፈርቱን ሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች የታሸጉ እና ማህተም የተደረገባቸው የዋጋ ማቅረቢያዎችን (Quotations) በግንባር በሚከተለው አድራሻ ማቅረብ ይችላሉ፡ ቦሌ መድኃኒዓለም፣ አቢሲኒያ ፕላዛ፣ 10ኛ ፎቅ
- የመጨረሻ ቀን፡ የጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን 11:00 ሰዓት ላይ
- ዘግይተው የሚመጡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
8. ተጨማሪ መረጃ
ሙሉውን የሥራ መግለጫ (Statement of Work)፣ የዲዛይን ማጣቀሻዎችን እና አጋዥ ሰነዶችን ለማግኘት በሚከተሉት አድራሻዎች ያግኙን፡
- ኢሜል: mihret.tsegaye@preciseethiopia.com ስልክ ቁጥር: +251 92 604 3198
- ወይም ሰነዶቹን ለመውሰድ በግንባር ቢሮ ድረስ መምጣት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
ድርጅቱ ማንኛውንም ማመልከቻ በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም ማስታውቂያው ከሚያበቃበት ቀን ቀደም ብሎ በቂ አመልካች ከተገኘ ያለምንም ማብራሪያ ሂደቱን በማንኛውም ደረጃ የማቆም መብት አለው።
አንድ ሚሊዮን ብርቱ
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን 11:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-06 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አንድ ሚሊዮን ብርቱ
- Published: Apr 25, 2026
- Posted at: 2026-04-25T08:20:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.