በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደቡብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጀሪካን፣ ፈሳሽና ደረቅ ሳሙናዎችን እንዲሁም ሌሎች የጽዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ሕጋዊ ተጫራቾችን ማጫረት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደቡብ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎችን ማለትም ጀሪካን ፈሳሽና ደረቅ ሳሙናዎችን እንዲሁም ሌሎች  የጽዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን  ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉትን ሕጋዊ ተጫራቾችን ማጫረት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት

1.በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ የተእታ ያለው(VAT ተመዝጋቢ የሆነ) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ም/ወቀረት ያለው፣እንዲሁም በመንግሰት ግዢ ((Egp ) በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ  የተመዘገበ፤

2. ከዚህ በፈት ጨረታ ተሳትፎ በጥራት አቅረቦ ላስረከበው መልካም የሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

4. ተጫራቹ የጨረታ ዋጋ 2 ፐርሰንት ማስከበሪያ ዋስትና በሲፕዩ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን እና ህጋዊነቱ ለ9ዐ ቀናት መሆን አለበት። የኢንሹራንስና ቼክ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቹ የሚጫረቱበትን ዋጋ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደቡብ ኢትዮጲያ ቅ/ጽ/ቤት ግዢ ፋይነንስና ንብረት አስተዳደሪ የመጀመሪያ ፎቅ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 (አሰር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታው ሰነድ አስተሻሸግ

1. ቴክኒካል እና ፋይናንሻል..

ኦሪጅናል (1) እና ኮፒ (1) በእናት ፖስታ ውስጥ አድርጎ በማሸግ የጨረታ ሰነዱን ማህበሩ ባዘጋጀ ውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. በአስረኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማህበሩ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡30 ማስገባት የምትችሉ ሲሆን 4፡30 ሳጥኑ ታሽጎ በእለቱ 4፡45 ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ትንሹ ስብሰባ አደራሽ ይከፈታል። ጫረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። ኤሌክትሮኒክ ጨረታ አየፈቀድም።

7.የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልግ በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ደቡብ ኢትየጲያ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስና ንብረት በአካል በመገኘት እንዲሁም በሁሉም ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመገኘት የማይመለስ አንድ ሺህ ብር(1000) በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000630160678 (ERCS SER BR Office) በመክፈል የጫረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች ሰነዱን የገዙበትን የባንክ አስሊፐ ጨረታን ለማስገባት ሲመጡ ይዘው መምጠት ይጠበቅባቸዋል።

8.መሰሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

ስልክ:- +251-11 083 179/+251-91 398 5801

አድራሻ፡ በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ አጠገብ፡

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወ/ሶዶ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን እስከ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-06 10:45
  • Bid opening (note): ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን እስከ 4፡45 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Apr 25, 2026
  • Posted at: 2026-04-25T10:04:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders