ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሃገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ-5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል
Description
የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራ የጨረታ ማስታወቂያ
ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሃገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ-5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንዲሁም የሰው ኃይል፤ ማሽን እና የግንባታ ግብዓቶችን ማሟላት የሚችሉ ስራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን በግልፅ ጨረታ ውድድር መሳተፍ ይችላሉ።
- በህንጻ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ -5(አምስት) እና ከዚያ በላይ ሆነው የታደሰ ፍቃድ ያላቸው፤
- የ2018 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት(VAT) ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
- በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ፍቃድ ያላቸው፤
- የመንግስት የግዢ አቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፤
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ 15(አስራ አምስት /ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ”ገነት ሆቴል " በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ እና ስራውን የመስሪያ ፋይናንሻል ሰነድ ለእያንዳቸው አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በተናጥል ለየብቻ በማሸግ በጥቅል በአንድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማደረግ እስከ አስራ አምስተኛው (15) ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አስራ አምስተኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መከፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ባሉበት በአስራ አምስተኛ (15) ከቀኑ 9፡00 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ካሳ ግራንድ ሞል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 011 550 4701 / 09 11 25 06 41 / 09 39 50 00 00
ገነት ሆቴል
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስተኛው(15) ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-11 15:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስተኛው(15) ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Genet Hotel Administration
- Buyer address: አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ገነት ሆቴል ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T10:07:38.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.