ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ስሙ ቫርኔሮ በሚባለው አካባቢ የሚገኙትን ባለ አምስት ወለል አምስት ህንጻዎች የውጭ እድሳት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ደረጃ ሰባት እና በላይ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ፈቃድ እና የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
ለዚህ ሥራ የተጠሩት ተጋባዥ ተጫራቾች
1. የሥራ ልምዳቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ እንዲያቀርቡ ይፈልጋል።
2. ለዘመኑ የታደሰ የንግድና ሥራ ፍቃድ ምዝገባ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ደብዳቤ ጋር በቀረበው የሥራ ዝርዝር መሰረት ለቀረቡት ሥራዎች የማቴሪያል እና የእጅ በአንድነት አካቶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነዱን ከማህበሩ ጽ/ቤት ዘውትር በሥራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡30) ከሚያዝያ 19 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት ቀናት መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ) በሲፒኦ ወይም በቢድ ቦንድ መልክ አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ጽ/ቤት በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከማቅረባቸው በፊት ህንጻዎቹ ያሉበትን ሁኔታ በአካል በመቅረብ እንዲጎበኙ ይመከራል። ተጫራቾች ለቴክኒክ ምዘና የሚያስፈልገውን የተሟላ ሰነድ በተለይም ከዚህ ቀደም ያከናወኑትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም የሚገልጹ ሰነዶችን ከህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሰነዶች ጋር አያይዘው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኤንቨሎፕ ውስጥ ከጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጋር በኤንቨሎፕ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የዋጋ ማቅረቢያው (ፋይናንሻል ፕሮፖዛል) በሌላ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። አሰሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ህብረት በካስማ የጋራ ህንፃ የቤ/ባ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-05-06 16:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ህብረት በካስማ የጋ/ህ/የቤ/ባ/ማህበር
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T10:09:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.