ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ
የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ LT/HT/HO/05/2026
1. ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምር አስከ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 - 6:00 እንዲሁም ክሰዓት በኋላ ከ7:30-10፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 - 5፡00 ድረስ “ሕዳሴ ቴስኮም አ.ማ ደብረዘይት መንገድ ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ አጠገብ ቴለ ጋራጅ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፦
አንድ ዋና /Original የጨረታሰነድ ለብቻው በሰም በታሽገ ፖስታ ታሽጐ፤
አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፣
በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ለሕዳሴ ቴሌኮም ኢማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 211 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 211 ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስሰከ ቁጥር 09 68-13 56 75 ወይም 09 68-27 12 91 መጠቀም ይችላሉ።
8. ሕዳሴ ቴሌኮም አማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-19
- Publishing entity: Hidase Telecom Share Company
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.