ከፍታ የወጣቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥራ ማህበር የአሰራር ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ ነባሩን የአሰራር ሂደት ክፍተት (gap analysis) እና የድርጅት መዋቅር ጥናት (organizational structure) ማስጠናት ይፈልጋል
Description
የድርጅታዊ መዋቅር ጥናት ጨረታ ማስታወቂያ
ከፍታ የወጣቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥራ ማህበር በተሻሻለው የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት ተመስርቶ በሃገር አቀፍ ሊያሰራ የሚችል የስራ ፍቃድ ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን አግኝቶ በሃገሪቱ ባሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በ 18 ከተሞች ላይ የቁጠባና ብድር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ማህበሩ የአሰራር ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ ነባሩን የአሰራር ሂደት ክፍተት (gap analysis) እና የድርጅት መዋቅር ጥናት( organizational structure) ማስጠናት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::
1. የሞያ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
2. የዘመኑ ግብር የከፈለ፤
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
4. ብቁ ባለሙያዎችን መድቦ በተሰጠው የግዜ ገደብ ስራውን ሰርቶ ማስረከብ የሚችል፣
5. የሚወዳደሩበትን የቴክኒካልና የፋይናሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስት በማሸግ ማስገባት የሚችል፣
6. እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች የሚጠየቁ መረጃወችን ማቅረብ የሚችል፣
7. ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን የስራ መመሪያ (TOR) በመውሰድ፣
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ እና ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ5 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡30-10፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
9. ጨረታው ምዝገባው በተጠናቀቀ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት መገኘት ካልቻሉ ጨረታው በተገኘው ሰው በጨረታ ከኮሚቴ ጋር ይከፈታል::
አድራሻ፡ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋስ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከፍታ የወጣቶች ኃ/የተ/መሰረታዊ የገ/ቁ/ብ/ኅብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት
ስልክ : 0116-67-42-66 / 0900 617 020
Tender details
- Deadline: 2026-05-02
- Publishing entity: Kefeta Youth Primary SACCO Ltd. Liab
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.