በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሞተር ሳይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

 በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለመስ/ቤቱ አገልግሎት

የሚውሉ፡- ሞተር ሳይክል በድጋሚ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው ፣
  3. የዘመኑ አቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
  7. ተጫራቾች በተራ ቁጥር የተገለፀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥና ከፍያ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 16 በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራች ዕቃውን ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቡታጅራ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማሰታውያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥናፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው ፣
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጐ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ በአዲሱ የችሎት አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፣
  10. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  11. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046 115 0711 ወይም 046 115 0097 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊዎች ላቀረቡት እቃዎች የእጅ በእጅ ደረሰኝ ተጠቃሚ ከሆኑ ከገቢዎች የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦርድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-11
  • Publishing entity: East Gurage Zone High Court
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders