የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- አ/አ/ፐ/ሰ/የሰ/ሃ/ል/ቢሮ/ግ/ጨ/ቁ/04/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እቃ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 ቋሚ እቃ
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ
1. ተጫራቾች -
ሀ. የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው
ለ. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት
ሐ. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
መ. የንግድ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት
ሰ.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ስፖርት ኮሚሽን ህንጻ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ቢሮ 10ኛ ፎቅ የግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
2.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት1፡ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ፡-
- ፋይናንሻል ኦርጅናል (ለብቻው)
- ፋይናንሻል ኮፒ (ለብቻው)
- ቴክኒካል ኦርጅናል (ለብቻው)
- ቴክኒካል ኮፒ (ብቻው) በፓስታ በማዘጋጀት የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን አይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት በሚቀርበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. አሸናፊ ድርጅት ባሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ7ኛ ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈረም አለበት።
7. በተራ ቁጥር 6 መሰረት ውል የማይፈጽም አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
8. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስፖርት ኮሚሽን ህንጻ 10ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-812-0635 አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Public Service and Human Resource Development Bureau
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.