የአብክመ ውሀና ኢነርጂ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የቢሮ መገልገያ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች (ሰርቨር) እቃ፣ fire wall & የተለያዩ የጅኦሎጅ የማዕድን የመስክ ጥናት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-10/2018
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ እና የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዮ ፕሮግራም በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የቢሮ መገልገያ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች (ሰርቨር) እቃ፣ fire wall ወዘተ እንዲሁም
- ሎት 2. የተለያዩ የጅኦሎጅ የማዕድን የመስክ ጥናት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1. እና ለሎት 2 ለእንዳንዳቸው ብር 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ ቀበሌ 07 ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት፣
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 87 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ።
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: የአብክመ ውኃና ኢነርጅ ቢሮ
- Bid bond: 150,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesMineral and Natural ResourcesGeotechnical Investigation & Laboratory TestingNetworking Equipment and InstallationSoftware Provision, Development and Web DesignLaboratory Equipment and ChemicalsTest & Measurement ToolsHand Tools and Workshop EquipmentAmharic2merkatoየአብክመ ውኃና ኢነርጅ ቢሮAmhara
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.