ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር (NCB 004/2018)
ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አራት ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማኅበር ዝቅ ብሎ ከበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዲን ኦፊስ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስም ሞልተው ከኦርጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታው መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ (በብር) |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
||||
|
1 |
ቋሚ እቃዎች ሎት 1 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
|
2 |
የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 2 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
|
3 |
የጽዳት አገልግሎት እቃዎች ሎት 3 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
|
4 |
ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጦች ሎት 4 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
|
5 |
የጤና መጠበቂያ ሎት 5 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
|
6 |
ኮምፈርት፣ አንሶላና ብርድ ልብስ ሎት 6 |
NCB 004/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4:30 |
በ15ኛው ቀን |
4:45 |
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰንጠረዡ መሠረት በኮሌጁ ዲን ኦፊስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማኅበር ዝቅ ብሎ በላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዲን ኦፊስ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0955 -11-11-11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።
7. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት
- Bid bond: 3,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.