የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት የተረከበውን ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረት አድራሻ

የንብረት ዝርዝር

የቦታ ስፋት (በሄክታር)

የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

የጨረታ ሁኔታ

የጨረታ ደረጃ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ/ ///ከተማ ወረዳ 08

ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፣ የህንፃ ግንባታዎች፣ የኤልክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት

1,678 ካሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት

122,600,997.28 /አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም/

ልዩ ድርድር

አንደኛ

ግንቦት 18 ቀን 2018 . ከጠዋት 400 እስከ 600 ሰዓት

ማሳሰቢያ፡-

1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከ4፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ ያስያዘውን ገንዘብ ይወርሳል፡፡

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፤ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡

6. አንዳንድ የድርጅቶች ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆነ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ክስ ለመክፈል ይገደዳል፡፡

7. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ፡፡

8. ባንክ ንብረቱን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል፡፡

9. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ያሳወቃል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ የማስፈፀም ሃላፊነት አለበት፡፡

10. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡

11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 / 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡

12.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ልማት ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-26
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders