ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለስልጠና ማዕከል የምግብ እና የሻይ፣ ቡና እንዲሁም ውሃ አቅርቦት ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ ስራ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
Commercial Nominees PLC
CN/NCB/31/18
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለስልጠና ማዕከል የምግብ እና የሻይ፣ ቡና እንዲሁም ውሃ አቅርቦት ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ ስራ ማሰራት ተፈልጓል።
በዚህም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ድርጅቶችን በሀገር ዓቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት የመሳሰሉትን የቴክኒክ ሰነዶች በተለየ የታሸገ ፖስታ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶኩመንት በተለየ ሁለተኛ የታሸገ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለስልጠና ማዕከል የምግብ እና የሻይ፣ ቡና እንዲሁም ውሃ አቅርቦት ግዥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.