የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት መንገድ ግንባታ እና ድልድይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመንገድ ፈንድ በጀት ድጋፍ በከተማችን የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራ ለማሰራት በ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

ስለዚህ ፡-

  1. የኮብልስቶን መንገድ ግንባታ ሥራ ከ ታደሰ አማረ ቤት አስከ አቶ ቻሴ ነጋ ቤት 150 ሜትር ሎት-1
  2.  የድሬኔጅ ግንባታ ሥራ ከ መኩሪያው ቤት አስከ አስፓልቱ መንገድ 93 ሜትር ሎት-2
  3.  የግራብል መንገድ ግንባታ ሥራ ሎት-3
  • ከ ቀበሌ ቤቱ አስከ የክራር ወንዝ ድልድይ 390 ሜትር እና
  • ከ አበራ ቤት አስከ አቶ በድሉ ቤት 220 ሜትር

ከላይ የተዘረዘሩት የመሰረተ ልማት ሥራዎች ባለሙያ ባወጣው ስፔስፊኬሽን መሰረት በ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት/መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. የታደስ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለግንባታ ሥራዎች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለ የኮብልስቶን መንገድ ግንባታ ስራ ለሎት- 1 ብር 70,342 ብር፤ ለ የድሬኔጅ ግንባታ ስራ ለሎት - 2 ብር – 30,913 ብር፤ የግራብል መንገድ ግንባታ ስራ ለሁለቱ ስራ ጠቅሎ በአንድ ለመስራት ለ ሎት-3 ብር – 12,900 ብር፤ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ሆኖ መረጃውን ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

3. የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 የስራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

4. የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም።

5. በማህበር ተደራጅተው ለሚወዳደሩ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከአደራጃቸው ተቋም ማምጣት አለባቸው።

6. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናቶች በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል እንዲሁም ከስራና ስልጠና ጽ/ቤት ተደራጅተው ለሚመጡ በነፃ የሚሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን።

7. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 22 ኛው ቀን ከቀኑ 4፡0 ሰዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናል ና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸዉ ቦታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ስዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙ ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ወይም ጨረታ ሰነዱን ፊርማና ማህተም በማድረግ በፖስታ ታሽጎ አንድ ወጥ የሆነ ኦርጂናል ና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

10. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉ ተወዳዳሪዎች ተጫራጮች በቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

11. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉ ተወዳዳሪዎች ተጫራጮች በቁጥር ቢያንስ ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲከ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

12. የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲከ ቼከ) በግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ወጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

13. ስለጨረታው አጠቃላይ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ይችላሉ።

14. የአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተጨማሪ ማብራሪያዎች እና ማሻሻያዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።

15. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

16. መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ / አድባንስ / የማይሰጥ መሆኑን ያሳውቃል።

17. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካለ በጽ/ቤቱ የውስጥ ሰሌዳ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን

18. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 117 0033/ 058 117 1208 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

19. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደባርቅ ከተማ አስተዳር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-19
  • Publishing entity: Debarek City Administration Infrastructure Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders