በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገቢዎች ሚኒስተር ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ኮድ (26-01B) ጠቅላላ ፕሮጀክቱን በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ኤጀንሲዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ ሥራውን ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር DCE/26-01B/OI/01/2026
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገቢዎች ሚኒስተር ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ኮድ (26-01B) ጠቅላላ ፕሮጀክቱን በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ኤጀንሲዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥበቃ ሥራውን ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-
1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
2. VAT የተመዘገባችሁበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ማቅረብ የምትችሉ
4. ከመንግስት የግብር ዕዳ ነፃ መሆናቸው (Tax Clearance) ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
5. ከፌደራል ፖሊስ የብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸውን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
6. በአዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የተመዘገቡበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
7. ተጫራቾች ለድርጅታቸው የታደሰ የኢንሹራንስ የገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
8. ተጫራቾች ዋጋቸውን ከመሙላታቸው በፊት ፕሮጀክቱን በአካል ተገኝተው መጎብኘት ይጠበቅባቸዋል።
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን የግዢ መመሪያ መሰረት በፕሮጀክታችን ትክክለኛ ስም መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የገቢዎች ሚኒስተር ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ኮድ (26-01B) (Defense construction enterprise The minster of revenues branch office project (26–01B)) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ አዳራሽ ይከፈታል።
12. የተጫራቾች ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተለያይቶ መቅረብ ይኖርበታል።
13. የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
14. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ጎፋ ስፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B)
(ጎፋ ካምፕ ገቢ ውስጥ)
ስልክ ቁጥር 09 12 15 42 45
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.