የፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን አዲስ በማስገንባት ላይ ላለው የህንፃ ቤተክርስትያን ልዩ ልዩ ሥራዎች በግራናይት በላይም ስቶን እና በባዛልት ዘመኑን በዋጀ የማሽን አቀራረጽ በማስቀረፅ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፈደፀቅጊ/ግንባታ /001/2018 (በድጋሚ የወጣ)
የፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን አዲስ በማስገንባት ላይ ላለው የህንፃ ቤተክርስትያን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ልዩ ልዩ ሥራዎች በግራናይት በላይም ስቶን እና በባዛልት ዘመኑን በዋጀ የማሽን አቀራረጽ በማስቀረፅ ለማሰራት ይፈልጋል።
- በለሰለሰ ሁኔታ የተቀረጸ የውጭ ገድግዳ ግራናይት ንጣፍ (ክላዲንግ)
- የበረንዳ አምዶች (column) የላይም ስቶን ንጣፍ (ክላዲንግ)
- የመስኮት እና የበር ፍሬም (በላይም ስቶን)
- የባዛልት ድንጋይ ቤዝ ፍሬም (ዘኮሎ)
- የወገብ አካፋይ ፍሬም መቀነት (በግራናይት)
1. የሥራው ዘርፍ
ተጫራቾች በሚከተሉት አማራጮች ተለይተው በቀረቡ ምድቦች ላይ መወዳደር ይችላሉ ፦
- ምድብ 1፦ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና ገጠማ
- ምድብ 2፦ የገጠማ/የእጅ/ ሥራ ብቻ
- ምድብ 3፦ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ብቻ
ተጫራቾች አንድም ሆነ ከዚያ በላይ በሆኑ ምድቦች ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ መስፈርቶች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድና የሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ።
- በተመሳሳይ የቤተክርስትያን ሥራዎች ላይ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው እና የ መልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃቸውን በፎቶግራፍ አስደገፈዉ ማቅረብ የሚችሉ።
- ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የድንጋይ ቅርፅ ማውጫ ማሽነሪና የወርክሾፕ አደረጃጀት ያላቸው።
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቤተክርስቲያኑ የህንጻ አሠሪ ኮሚቴ ጽ/ቤት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ) በስራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ 7፡30 እስከ 11፡30) መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በሁለት ቅጂዎች (አንድ ዋናና ሁለት ቅጂዎች) ለየብቻ በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና በ ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
4. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ) በአየር ላይ ቆይቶ ፣ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ጽ/ቤት ይከፈታል።
5. ልዩ ማሳሰቢያ
- ማንኛውም ተጫራች የግንባታ ሂደት ጉብኝት (Site Visit) የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን፤ የቴክኒክ ምዘና ውጤታቸው ከ70% በላይ ለሆኑ ተጫራቾች ብቻ የፋይናንስ ሰነዳቸጡ የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች የስራ ቦታ (work shop) እና የሰሩዋቸው ስራዎች በቴክኒካል ግምገማ ወቅት በጨረታ ኮሚቴ ይጎበኛሉ።
- የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ግምገማ ድምር ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያመጣ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለናሙና የሚሆን የግራናይት ቅርፅ በደብሩ ግቢ ውስጥ ሠርተው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
- ቤተከርስቲያኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስልክ ቁጥር 0911223523/0911231951
የፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ) በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-08 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ) በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Apr 29, 2026
- Posted at: 2026-04-29T09:20:31.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.