የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ግንባታዎችን ማስገንባት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
1/ኛ አንድነት ቀበሌ ከአቶ ኪዳኔ ማሞ መኖሪያ ቤት እስከ መቱ ኪያዙ መኖሪያ ቤት ድረስ 250 ሜትር የዲች ቦይ ጥገና እና ብዛት 4(አራት) 10 2ሜ አዲስ እስላቭ ካልቨርት ስራ
2/ኛ አንድነት ቀበሌ ከቤተሰብ ህጻናት ማቆያ እስከ ጀማል መኮንን መኖሪያ ቤት 134 ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ግንባታ
3/ኛ የእንቁላል ዶሮ እርባታ ሼድ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩትን ተጫራቾች በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
1ኛ/ተጫራቾች በተሰማሩበት የግንባታ ስራ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2ኛ/ተጫራቾች የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
3ኛ/ተጫራቾች የቫት (የተጨማሪ እሴት ታከስ) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
4ኛ/ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
5ኛ/ተጫራቾች የ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ የገቢ ኪሊራንስ ማቅረብ።
6ኛ/ተጫራቾች ማህበራት ከሆኑ ህጋዊ ሰውነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
7ኛ/ተጫራቾች ማህበራት ከሆኑ ከአደራጅ መ/ቤት ብዛት 5 የማህበሩ አባላት ስም ዝርዝር ማቅረብ አለባቸው።
8ኛ/ተጫራቾች ማህበራት ከሆኑ የ2018 የታደሰ ደረጃ 9 (ዘጠኝ) ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
9ኛ/ተጫራቾች ማህበራት ከሆኑ ከ3-5 የቲቪቲ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
10ኛ/ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ የሚከፈት ይሆናል።
11ኛ/ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12ኛ/ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ቴ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በመቅረብ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
13.ኛ/ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
14ኛ/ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ለተ.ቁ/1/ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ለተ.ቁ /2/ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ለተ.ቁ /3/ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቴፒ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
15ኛ/ በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስሪያ ቤቱ ጨረታውን መከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
16.ኛ/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-16
- Publishing entity: Tepi City Administration Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 29, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.