በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በ2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
(Addis Ababa City Administration Revenue Bureau Guellele Sub City Small Tax Payers Branch Office) – 002/2018
ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 2፡- የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3፡- ህትመት
- ሎት 4፡- ደንብ ልብስ
- ሎት 5፡- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፋክስ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ስካነር እና ኤሌክትሮኒክ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 6፡- ቆሎ
- ሎት 7 ፡- የታሸገ ውሃ በ2018 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ ወይም (online የተመዘገቡ)፣
3. የ6 ወራት ያላለፈው የጨረታ መወዳደሪያ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በመ/ቤቱ የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልተጠቀሰ ዋጋው ተ.እ.ታን(VAT) እንዳካተተ ተደርጉ ይወሰዳል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት።
7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ አጠገብ ቃሲም ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ የግዥ አገልግሎት ቡድን በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክ/ከተማ አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000378561829 (4054) ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት ሰነዱን መግዛት ይቻላል፣
8. ተጫራቾች ፋይናንሻል እና የቴክኒክ ሰነድ ዋናውን ዶክመንት፣ ፎቶ ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ 2% ለየብቻው በታሸገ እንዲሁም የድርጅቱ ስም፣ስልክ ቁጥራቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን፣የድርጅቱን ማህተም እና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ምድብ በመጻፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ጊዜው የሚያበቃው ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ከበብ አጠገብ ቃሲም ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ በግዥ አገልግሎት ቡድን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ የግዥ አገልግሎት ቡድን ውስጥ ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1፣2፣3፣4 እንዲሁም ከሎት 4 እስከ 6 ላሉት የኮንትራት ስምምነት ለሚጠየቀው ብቻ ለእያንዳንዱ ምድብ ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር/ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ምድብ /ሎት/ ግን የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤ ጨረታውን ለማዛበት የሚሞክር ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
12. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፣
13. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ዕቃ ዋጋው 10% ማስያዝ መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
14. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ዕቃዎቹን መ/ቤቱ ስቶር ድረስ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በማጓጓዝ ያቀርባል።
15. ለዓመታዊ የኮንትራት ዕቃዎችና አገልግሎት አሸነፊ ድርጅት ከመ/ቤቱ ውል ከገባበት ጀምሮ ለተከታታይ 6 ወራት የተጠየቀው አገልግሎት ሆነ ዕቃዎች በቀረበው ዝርዝር ስፔስፌኬሽን መሰረት እያቀረበ ያለ ከሆነ በወቅቱ የገበያ ጥናት ተደርጉ የዋጋ ማስተካከያ ሊያደርግ ይችላል።
16. በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ አካላት ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይገባቸዋል፡፡ የደብዳቤው ይዘትም ተጫራቹ በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ አቋርጦ ቢወጣ ለሚፈጠረው ክፍተት ዋስትና የሚሰጥ መሆን ይገባቸዋል፤
17. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በተገለጸው የመጫረቻ የሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ ተቀባይነት የለውም፤ በተጨማሪም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈጸሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
18. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ሆነ የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚፅፉት ማንኛውም አስተያየት ተጨባጭ እና ሊረጋገጥ የሚችል መሆን ይኖርበታል፤ግልፀኝነት በሚጎድልበት ጉዳይ ላይ ተጫራቾች መከራከር አይችሉም።
19. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርቡ ዋጋ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል። ሆኖም ግን የኮንትራት ስምምነት ዕቃ ግዥ ሆነ አገልግሎትን አይመለከትም።
20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ” እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃ ብዛት 20% ቀንሶ ወይንም ጨምሮ ከአሸናፊ ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
21. ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር/ 011-126-50-06 ወይም 011-156-71-98 በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ማሳሰቢያ፤- ቅዳሜ እስከ 11:00 ሰዓት ለስራ ክፍት ሆኖ ይውላል፤ እንደ ስራ ቀንም ይቆጠራል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-13
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Revenue Bureau Gullele Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 29, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.