Amharic
የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ሪሶ ማሽን፣ ኮፒ ማሽን፣ እስካነር እና የመሳሰሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4
የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን ሪሶ ማሽን፣ ኮፒ ማሽን፣ እስካነር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1-ሪሶ ማሽን፣ ኮፒ ማሽን፣ እስካነር፣ ቴሌቭዥን 86"
- ሎት 2-ፕሪንተር፣ ኮምፒውተር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቲን (TIN) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ሎት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ሎት 2 ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የተከታታይ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የመዝጊያ ቀን ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን በ5 ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ ፡-አዳማ ወንጂ መንገድ የኦሮሚያ አዳሪ ት/ቤት ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር – 022 212 3599/ 09 11-65 97 49/
09 11-06 94 85 መደወል ይቻላል።
የኦሮሚያ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Oromia Occupation Competency Assessment and Certification Agency
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: May 01, 2026