አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ አገልግሎቶች የሚውሉ 3 የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖች፣ ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን እና የመኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) እና 1147/2011 መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚፈለግትን ክፍያ ከፍሎ ንብረቱን ካልተረከበ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪ/መያዣ ስጪ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታው የሚካሄደው አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ B 4ኛፎቅ የፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 ወይም 011 515 1153 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ ፡- በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱት መጋዘኖች እና ማሽነሪዎቹ ተነጣጥለው አይሸጡም።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው አጠቃላይ ስፋት በካ.ሜ |
የካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
|
1 |
ቡሬ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ለኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ አገልግሎቶች የሚውሉ 3 የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖች |
30,000 (ሰላሳ ሺህ) |
ገ/መ/አስ/መ14/2013 |
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስሜን ሽዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ |
የመጋዘኖቹ በድምሩ ብር 61,854,744.00 |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
|
ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን
|
---- |
የደረሰኝ ቁጥር 063፣ 057፣ 076፣ 081 እና 053
|
የማሽኑ ብር 12,000,000.00
|
|||||||
|
2
|
ምሳሌ እግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
|
ተበዳሪው
|
ለኢንዱስትሪ አገልግሎቶች የሚውሉ 5 የተለያየ ስፋትያላቸው መጋዘኖች |
50,000 (ሀምሳ ሺህ) |
ገ/መ/አስ/መ07/2013 |
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሽዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ |
የመጋዘኖቹ በድምሩ ብር 63,735,635.18 |
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
|
ዘመናዊ የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ማሽን
|
---
|
የደረሰኝ ቁጥር SIYERO1704162, SLYE201709160, SLYE201710161A እና 17F0502 |
የማሽኑ ብር 15,000,000.00
|
|||||||
|
3 |
አቶ ኢማሙ ሩቤ ዋሾ |
ተበዳሪው |
የመኖሪያ ቤት |
199.75 |
የካርታ ቁጥር 0413789
|
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን ዴራ ከተማ ቀበሌ 02 |
1,803,700.07
|
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም.
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
|
4 |
ቢዘዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ ኑሩ ሸፈቀ
|
መኖሪያ ቤት
|
200
|
BRU/4380/2000
|
ሸገር ከተማ፣ ቡራዩ ክ/ክተማ
|
3,850.541.38
|
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-02 16:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: May 03, 2026
- Posted at: 2026-05-04T09:38:00.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.