በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል መጠኑ 40,000 (አርባ ሺህ) ቶን ለሶስት ወራት አቅርቦት ጊዜ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀገር ውስጥ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ / 17/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል መጠኑ 40,000 (አርባ ሺህ) ቶን ለሶስት ወራት አቅርቦት ጊዜ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው የሚሳተፉ ድርጀቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባና የታደሰ የንግድ ፈቃደ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ተከስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት ጋራድ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.RO.) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በእለቱ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ፡011 442 0216

ፋክስ፡ 011 442 0688

አዲስ አበባ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-05-12 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mugher Cement Factory
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 2,000,000.00 ብር
  • Bid document price: 575.00 ብር
  • Published: May 04, 2026
  • Posted at: 2026-05-06T09:30:05.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders