የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለፓምፕ ቴስት ስራ እና ለወርክ ሾፕ አገልግሎት የሚውሉ የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ጥሪ
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር NCB WWC/14/2018
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) ለፓምፕ ቴስት ስራ እና ለወርክ ሾፕ አገልግሎት የሚውሉ የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 14/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods/ |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርመራ
|
|
1 |
ሎት_1 |
Difference types of machine |
Set |
04 |
|
|
2 |
ሎት-2 |
submersible pump with all accessories And pump power cable |
Set/meter |
ጥቅል |
|
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት። ተጫራቾች እነዚህንና ልሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ88 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት1- ብር 350,000.00 /ሶስት መቶ አምሳ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 250,000.00 /ሁለት መቶ አምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክትሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ኮርፖሬሽነ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር 058222-14-79 መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
8. ማስሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጅ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
አድራሻ:-
ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲናስ ጠቅሳላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106, ስልክ ቁጥር 0582221479
ባህርዳር
የውኃ ስራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-23 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Water Works Corporation
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: May 04, 2026
- Posted at: 2026-05-06T10:14:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.