የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 ጠቅላላ ሥራ እና መንገድ ሥራ ተቋራጭ GC/RC-2) የሆኑ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳትፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን የኮምቦልቻ እና ባህር ዳር ኤርፖርቶች የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራ (Design-Build of Emergency Access Road Construction at Kombolcha and Bahir Dar

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T614

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 ጠቅላላ ሥራ እና መንገድ ሥራ ተቋራጭ GC/RC-2) የሆኑ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳትፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን የኮምቦልቻ እና ባህር ዳር ኤርፖርቶች የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራ (Design-Build of Emergency Access Road Construction at Kombolcha and Bahir Dar Airports) በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ሁለት ፕሮጀክቶች፤ፕሮጀክት 1፡ ባህር ዳር ኤርፖርት፣ ፕሮጀክት 2፡ ኮምቦልቻ ኤርፖርት።

ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T614 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ – (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለሁለቱም ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

የጨረታ ሰነዶች ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ተከታታይ ቀናት ጸንተው ሊቆዩ ይገባል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 180 ተከታታይ ቀናት ይሆናል:: ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሰኔ 1, 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል

ወ/ሮ ብርቱካን ሰሙ

ስልክ ቁጥር 011-517-4552

ኢ.ሜይል: birtukans@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 04, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders